“የሀገርን ክብር አሳልፈው ለሚሠጡ ኃይሎች የከተማችን ሕዝብ ቦታ የለውም” ከንቲባ ሙሐመድአሚን የሱፍ

10
በኮምቦልቻ ከተማ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ እና የጥፋት ኃይሎችን የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
​በሰልፉ ላይ የተገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች ሠራዊቱ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር እና የሕግ ማስከበር ዘመቻውን ስኬታማ ለማድረግ እያደረገ ያለውን መስዋዕትነት የሚያበስሩ እና ደጀንነታቸውን የሚያረጋግጡ መልዕክቶችን አሰምተዋል።
የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ አሚን የሱፍ ሕዝቡ በአንድነት በመውጣት ያሳየው ደማቅ ድጋፍ የከተማው ነዋሪ ለሀገር ሰላም እና ሉዓላዊነት ያለውን ጽኑ አቋም የሚያንጸባርቅ ነው ብለዋል።
የሀገርን ጥቅም እና ክብር አሳልፈው ለመስጠት ለሚሠሩ ጸረ ሰላም ኃይሎች የከተማችን ሕዝብ ቦታ የለውም ያሉት ከንቲባው የኮምቦልቻ ከተማ ሕዝብ ከጀግናው የሀገር ጋሻ ሠራዊት ጎን በመቆም ሰላሙን አጽንቶ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።
​በብልጽግና ፓርቲ የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙሉጌታ አቢ ሰልፉ የሕዝቡን አንድነት እና የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የጸጥታ ኃይል እየከፈለ ላለው መስዋዕትነት እውቅና የሚሰጥ ነው ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ሕዝባችን በአደባባይ በመውጣት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያለውን ድጋፍ አሳይቷል፤ ለፀረ-ሰላም ኀይሎችም ቦታ እንደሌለው አረጋግጧል” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ
Next article“‎የደብረ ማርቆስ ከተማ ሕዝብ ጥፋትን እና ትርምስን ፈጽሞ ተቃውሟል፤ የሰላም እና የሕግ መከበር መሻቱን በዓደባባይ ገልጿል” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ መልካሙ ሽባባው