የኤፍራታ እና ግድም ወረዳ አጣዬ ከተማ ነዋሪዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊቱን የሚደገፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች በመልዕክታቸው፦

የባሕር በር ባለቤትነታችን በልጆቿ መስዋዕትነት እውን ይኾናል፣

ለድል የተወለደው ሠራዊታችን አለኝታችን ነው፤

ከግድቡ ወደ ወደቡ እንሸጋገራለን፤

የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንን እንደግፋለን፤

ሀገርን ለማጽናት እና ለማበልጸግ ከመንግሥት ጎን እንሰለፋለን፤

መንግሥት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች እንደግፋለን የሚሉ ይገኙበታል።