በደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማ የመከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

3
በምሥራቅ ጎጃም ዞን የደባይ ጥላት ግን ወረዳ እና የቁይ ከተማ ነዋሪዎች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ድጋፍ በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጹ ነው።
በሰልፉ እየተሳተፉ የሚገኙት ነዋሪዎች የሀገርን ሰላም፣ ደኅንነት እና አንድነት የሚጎዱ እንዲሁም ልማትን የሚያደናቅፉ አካላትን አውግዘዋል።
የኢትዮጵያን ሰላም እና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የመከላከያ ሠራዊት ለሚያደርገው የሕግ ማስከበር ሥራ ያላቸውን ድጋፍም ገልጸዋል።
ሕዝቡ ሰላምን በማጠናከር፣ ሕግን በማክበር እና በጋራ በመቆም የኢትዮጵያን ሰላማዊ የወደፊት ጉዞ ለማጽናት ያለውን ፍላጎት ለማሳየት የተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ መኾኑም ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገር አለኝታ ነው” የሸዋሮቢት ወረዳ ነዋሪዎች
Next articleበእነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ አሥተዳደር የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን የሚደገፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።