የሕዝቡን ፍላጎት መሠረት በማድረግ ሰላም እና የሕግ የበላይነት የተከበረበት እንዲሁም ልማት የተፋጠነበት ወረዳ ለመፍጠር ይሠራል።

2
በሰሜን ሽዋ ዞን በመርሐቤቴ ወረዳ ፌጥራ ከተማ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
በሰልፉ ላይ የመከላከያ ሠራዊቱን የሕግ ማስከበር ዘመቻ እና የሀገርን ሉዓላዊነት የማስከበር ጥረት የሚደግፉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
በተለይም “የኅብረ-ብሔራዊነታችን አርማ፣ የአንድነታችን እና የክብራችን መገለጫ የኾነውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት እንደግፋለን” እና “የባሕር በር ባለቤትነታችን እውን ይኾናል” የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል።
የመርሐቤቴ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ጌታው በላይግዛው ሠራዊቱን እና ጥምር ጦሩን መደገፍ የሁሉም ዜጋ ኀላፊነት መኾኑን አሳስበው፤ የሕዝቡን ፍላጎት መሠረት በማድረግ ሰላም እና የሕግ የበላይነት የተከበረበት እንዲሁም ልማት የተፋጠነበት ወረዳ ለመፍጠር እንደሚሠራ ገልጸዋል።
የሰልፉ ተሳታፊ ነዋሪዎች በበኩላቸው አሁን ያለው ሰላም እና ነፃነት በመከላከያ ሠራዊቱ እና በጥምር ኀይሉ መስዋዕትነት የተገኘ በመኾኑ ለሠራዊቱ ያላቸውን አጋርነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበኮምቦልቻ ከተማ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
Next article“ለድል ከተወለደው የመከላከያ ሠራዊት ጎን ነን” የጣርማ በር ወረዳ እና የደብረ ሲና ከተማ ነዋሪዎች