በኮምቦልቻ ከተማ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

3
የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች ወደ አደባባይ በመውጣት የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም የባንዳዎች ሴራ ይፈርሳል፤ የኢትዮጵያ አንድነት እና ሰንደቅዓላማው ከፍ ይላል፤ ለድል የተወለደው መከላከያ ሠራዊት
አለኝታችን ነው፤ የኮምቦልቻ ሕዝብ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ነው፤ የሀገር መከላከያ የሠራዊት የነፃነታችን መሠረት ነው፤ የከተማችን እና
የሀገራችንን ሰላም በጋራ እንጠብቃለን፤ መከላከያ ሠራዊታችን የኅብረ-ብሔራዊነታችን ማሳያ ዓርማችን ነው የሚሉ እና ሌሎችም መልዕክቶች በሰልፈኞቹ እየተላለፉ ነው።
የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች በሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች ናቸው።
በደጀን አምባቸው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ እና በዱርቤቴ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
Next articleየሕዝቡን ፍላጎት መሠረት በማድረግ ሰላም እና የሕግ የበላይነት የተከበረበት እንዲሁም ልማት የተፋጠነበት ወረዳ ለመፍጠር ይሠራል።