“በማይነጥፈው የመከላከያ ሠራዊት ጀግንነት የሀገራችን ክብር ከፍ ይላል” የአልቡኮ ወረዳ ነዋሪዎች

5
የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ እና ሀገር ለማፍረስ የሚልኩ እና የሚላላኩ ጠላቶችን የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በደቡብ ወሎ ዞን በአልቡኮ ወረዳ በጦሳ ፈላና ከተማ ተካሂዷል።
ሰላማዊ ሠልፈኞቹ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ክብር እና ደጀንነታቸውን የሚያመላክቱ ልዩ ልዩ መልዕክቶችንም አስተላልፈዋል።
የባዕዳንን ሴራ ተሸክመው ሀገር ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ ባንዳዎችን በጽኑ እናወግዛለን ብለዋል ሠልፈኞቹ።
ሴራ እና ባንዳነት ይፈርሳሉ፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እና አንድነት በመከላከያችን ክቡር መስዋዕትነት ከፍ ይላሉ ብለዋል።
በማይነጥፈው የመከላከያ ሠራዊታችን ጀግንነት እና ተጋድሎ የሀገራችን ክብር ከፍ እናደርጋለን ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ጥራት ያለው ስታትስቲክስ ሳይንሳዊ ፈጠራን ለማሳደግ ወሳኝ ነው” የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Next articleሀሰተኛ መረጃን በመከላከል የሰውን ልጅን ሰብዓዊ ክብርን በመጠበቅ ይገባል።