“ጥራት ያለው ስታትስቲክስ ሳይንሳዊ ፈጠራን ለማሳደግ ወሳኝ ነው” የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

15
10ኛው የአፍሪካ ስታቲስቲክስ ኮሚሽን ጉባኤ (ስታትኮም-አፍሪካ) በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እየተካሄደ ነው፡፡
ጉባኤውን የከፈቱት የኤፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የዲጂታል መሠረተ ልማት ማደግ የስታቲስቲክስ መረጃን ለማግኘት ወሳኝ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የዲጂታል ገንዘብ ዝውውር ላይ ከፍተኛ ለውጥ አምጥታለች፤ ይህም መረጃን በምን ያክል መጠን እንደያዝን ማሳያ ኾኖ ያገለግላል ነው ያሉት፡፡
ስታቲስቲክስ ፓሊሲ አውጭዎች ግልጽ እና በመረጃ ላይ የተደገፈ ውሳኔ አንዲያሳልፉ የሚረዳቸው መሳሪያ ሲኾን መረጃ አንዲያድግ አንዲሁም ሕዝብ ተቋማዊ እምነት አንዲያሳድር ያደርጋል ነው ያሉት፡፡
ሳይንሳዊ ውሳኔም በመረጃ ላይ መሰረት አድርገው እንዲወስኑ እንደሚያስችልም አስገንዝበዋል። ፕሬዝዳንቱ ጥራት ያለው መረጃን ለማሳደግ እርስ በእርስ መረዳዳት እና መማመር ወሳኝ ነው ፤ ኢትዮጵያም ከሁላችሁም ትማራለች ያላትንም ልምድ ታጋራለች ብለዋል።
ከ10ኛው የአፍሪካ ስታቲስቲክስ ጉባኤ ጋር 12ኛው የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የጂኦ-ስፓሻል መረጃ አሥተዳደር ለአፍሪካ ሥብሠባም አብሮ እየተካሄደ ይገኛል።
የአፍሪካ ስታቲስቲክስ ጉባኤ እስከ ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም የሚካሔድ መኾኑ ታውቋል፡፡
ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“የክልሉን ልማት ለማሳለጥ በፍጥነት፣ በፈጠራ እና በጥራት ተሠርቷል” ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)
Next article“በማይነጥፈው የመከላከያ ሠራዊት ጀግንነት የሀገራችን ክብር ከፍ ይላል” የአልቡኮ ወረዳ ነዋሪዎች