
የሀገራችን መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ አለኝታ እና ኩራት የመጨረሻ ምሽግ ነው።
ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሀገሩ እየከፈለ ያለውን መስዋዕትነት የሚደግፍ እና የውጭ እና የውስጥ ጠላቶችን እኩይ ተግባር የሚቃወም ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በደቡብ ወሎ ዞን ጊምባ ከተማ ተካሂዷል።
የጊምባ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ እያሱ ዓባይ የሀገራችን መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ሰላም ለማጽናት በትውልድ የሚዘከር ተግባር እያከናወነ ነው ብለዋል።
ሠራዊቱ የሀገር ሰንደቅ ዓላማ እንዳይደፈር ራሱን ከፊት እያስቀደመ የጽናት ጉዞውን በድል አድራጊነት መቀጠሉን ነው አቶ እያሱ የተናገሩት። ሀገርን የሚፈታተኑ የውጭ እና የውስጥ ጠላቶችን ሴራ እያከሸፈ፤ ሰንደቁን ከፍ አድርጎ እየሰቀለ፣ የሀገርን አሸናፊነት በድል አድራጊነት እያበሰረ፤ በከፍታ ማማ ላይ ይገኛል ነው ያሉት።
ለሀገር እና ለሕዝብ ደኅንነት ሲል ደሙን እያፈሰሰ፣ አጥንቱን እየከሰከሰ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሕዝባዊነቱን እና ልማታዊነቱን የሚያሳዩ እጅግ አኩሪ ተግባራት ማከናወኑን ከንቲባው አስረድተዋል።
በሕዝብ እና በመንግሥት ጥረት የሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ለአፍታም ቢኾን አይደናቀፍም ነው ያሉት።
አሚኮ ያነጋገራቸው የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች የመከላከያ ሠራዊታችን የሕዝቡን ደኅንነት ለማስከበር ሲል በብቃት የተወጣቸው አንጸባራቂ ገድሎች አሉት ብለዋል። “ሕይወቱን ለሀገሩ የሰጠ አሸናፊ ሠራዊት ስላለን ኩራት ይሰማናል” ነው ያሉት የሕዝባዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች።
ሠራዊቱ በሰላሙ ጊዜ በልማቱ ለጉልበቱ እንደማይሰስት የገለጹት የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች በበርካታ የልማት ሥራዎች ላይ የዜግነት ድርሻውን እየተወጣ መኾኑንም ጠቁመዋል።
የሕዝብ ልጅ የኾነው መከላከያ ሠራዊት እያስመዘገበ ባለው አንጸባራቂ ድል መደሰታቸውን ነው የተናገሩት።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ደሴ #ጥቅምት_11_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ፦ አንተነህ ጸጋዬ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
