በኩታበር ወረዳ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ።

74

 

በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ እና ሀገር ለማፍረስ ከጠላቶች ጋር የሚላላኩ አካላትን የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።

በሰልፉ ላይ የተሳተፉት የአካባቢው ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አክብሮት እና ደጀንነት የሚያንፀባርቁ ልዩ ልዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

ሰልፈኞቹ “የባዕዳንን ሴራ ተሸክመው ሀገር ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ ባንዳዎችን በጽኑ እናወግዛለን” ብለዋል።

በሠልፉ ላይ ከተላለፉ መልዕክቶች መካከልም፦

👉“ሴራና ባንዳነት ይፈርሳሉ፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እና አንድነት በመከላከያችን ክቡር መስዋዕትነት ከፍ ይላል!”

👉“ባንዳ ለሆዱ፤ መከላከያ ሠራዊታችን ለሕዝቦች ክብር እና አንድነት!”

👉“መከላከያ ሠራዊታችን የኅብረ ብሔራዊነታችን ማሳያ አርማችን ነው!”

“በመከላከያ ሠራዊታችን የማይነጥፍ ጀግንነት እና ተጋድሎ የሀገራችንን ክብር ከፍ እናደርጋለን!” የሚሉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

የሰልፉ ተሳታፊዎች የሀገርን ሰላም እና አንድነት ለማስጠበቅ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን እስከመጨረሻው እንደሚቆሙም አረጋግጠዋል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ደሴ #ጥቅምት_11_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ኢትዮጵያ ባንዳን እና ባዕዳንን የማንበርከክ ታሪኳ ዛሬም ይደገማል” የአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች
Next article“ሕይወቱን ለሀገሩ የሰጠ አሸናፊ ሠራዊት ስላለን ኩራት ይሰማናል” የጊምባ ከተማ ነዋሪዎች