
በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች “ሉዓላዊነት በጀግኖቻችን መስዋዕትነት፤ ከኅብረ ብሔራዊ አንድነት እስከ ባሕር በር ባለቤትነት” በሚል መሪ መልዕክት ለመከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል።
ነዋሪዎቹ በሰልፉ ላይ፦
👉”ሴራ እና ባንዳነት ይፈርሳሉ፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እና አንድነት ከፍ ይላሉ”
👉”ከግድቡ ወደ ወደቡ፤ መከላከያ ሠራዊታችን የኅብረ ብሔራዊነታችን ማሳያ አርማችን ነው”
👉”ለመከላከያ ሠራዊታችን፣ ለፌዴራል እና ለክልላችን የጸጥታ ኀይሎች ለከፈሉት መስዋዕትነት ክብር እንሰጣለን”
👉”የኢትዮጵያን ጠላቶች እየደመሰስን ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ እናደርጋለን፤ መንግሥት ለሰላም ማስከበር የሚወስዳቸውን እርምጃዎች እንደግፋለን” የሚሉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
ሀገራቸውን ክደው ከውጭ ኀይሎች ጋር በማበር የሚንቀሳቀሱ አካላት የሕዝብ እና የሀገር ጠላቶች መኾናቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ሀገር አፍራሾችን እና የውጭ ጠላቶችን እየመከተ ሉዓላዊነትን እያስከበረ ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ሁልጊዜም ደጀን በመኾን አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
የአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መሐመድ ሰይድ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር የልማት ግስጋሴዋን እያረጋገጠች ትገኛለች ብለዋል።
ሀገር እንድትጸ እያደረገ ያለው የመከላከያ ሠራዊት የኅብረ ብሔራዊነት እና የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች መገለጫ መኾኑንም አክለው ገልጸዋል።
ጽንፈኞች እና ተላላኪዎች ከባዕዳን ተልዕኮ ወስደው ሀገር ለማፍረስ የሚያደርጉት ጥረት እንደማይሳካ ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ያሳካችውን ስኬት በባሕር በር ባለቤትነትም በመድገም የልማት ጉዞዋን አጠናክራ የምትቀጥል መኾኑን ተናግረዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ደሴ #ጥቅምት_11_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ፦ አበሻ አንለይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
