
ሰልፉ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ፣ የግብጽ፣ ሻዕቢያ እና የሕገወጡን ሕወሃት ሴራዎች ደግሞ የሚያወግዝ ነው። “ባዕዳ እና ባንዳ
ቢደራጁም የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ክንድ አለና ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ አይችሉም” ብለዋል ነዋሪዎቹ በሰልፋቸው።
ሰልፉ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ለክልሉ የፀጥታ ኃይል አጋርነትን የሚያሳይ ነው።
አደባባይ የወጣው ሕዝብ የታሪካዊ ጠላቶች ተላላኪ የሆኑ ጽንፈኞችን እኩይ ዓላማ በጀግኖች የፀጥታ ኃይሎች ላይመለስ መከሸፉን በመግለጽ፣ እስከመጨረሻው ከሠራዊቱ ጎን እንደሚቆም እያወጀ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
