በደሴ ዙሪያ ወረዳ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ እና የጠላቶችን ሴራ የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ።

8
በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ዙሪያ ወረዳ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፉ እና የውስጥ እና የውጭ የኢትዮጵያ ጠላቶችን የሚያወግዙ ሕዝባዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።
በሰልፉ ላይ የተሳተፉት የወረዳው ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ጽኑ ደጀንነት በአደባባይ አረጋግጠዋል።
ሰልፈኞቹ ለሕገወጡ የሕወሃት ቡድን፣ ለሻዕቢያ እንዲሁም ለግብጽ የላኪ እና ተላላኪነት ሴራዎች ፈጽሞ እንደማይበገሩ በመግለጽ ባዳዎችን እና ተላላኪዎችን አውግዘዋል።
ሀገራዊ አንድነትን አና ሉዓላዊነትን የሚያጠናክሩ መልዕክቶችንም አስተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበባሕር ዳር ከተማ ከአዲሱ የዓባይ ድልድይ እስከ ከመድኃኒዓለም ቤተ ክርስትያን የሚዘልቅ የ7ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ተጀመረ።
Next articleየመቅደላ ወረዳ ነዋሪዎች ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።