
በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና መካነሰላም ከተማ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ እና የግብጽ፣ ሻዕቢያ እና ሕገ ወጡን ሕወሃት ሴራ የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በሰልፉ ላይ የተገኙ በርካታ የከተማዋ እና የአካባቢው ነዋሪዎች የሀገርን ሰላም እና ደኅንነት ለማስጠበቅ መስዋዕትነት እየከፈለ የሚገኘውን የመከላከያ ሠራዊት እንደሚያግዙ ገልጸዋል።
ሠልፈኞቹ “የሀገራችንን ሰላም ለማወክ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር የተሰለፉ ኀይሎችን በጽኑ እናወግዛለን!” የሚሉ እና ሌሎች ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ መፈክሮችን አሰምተዋል።
የሰልፉ ተሳታፊዎች አክለውም የሀገርን ሰላም ማደፍረስ እና ከውጭ ኀይሎች ጋር በመተባበር ሀገርን ለማዳከም የሚደረጉ ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች እንደሚቃወሙ እና ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመቆም አጋርነታቸውን እንደሚሰጡ አጽንኦት ሰጥተው አረጋግጠዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
