
ሀገር የማያስነካ፤ ሉዓላዊነቱን በጀግንነት የሚጠብቅ፤ ከኢትዮጵያም አልፎ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሀገር ዘብ ነው የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት።
የሀገር ዋልታ የኾነውን መከላከያ ሠራዊት የሚደግፉ፣ ሀገርን ለመበደል የሚውተረተሩ የሀገር ውጭ እና የውስጥ ላኪና ተላላኪ ጠላቶችን ደግሞ የሚያወግዙ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ዛሬ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ይካሄዳሉ።
አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎችን እና የሚተላለፉ መልእክቶችን ወደተከታይቹ ያደርሳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
