
በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ በጫካ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች በመንግሥት የቀረበላቸውን የሰላም አማራጭ ተቀብለው መካነ ኢየሱስ ከተማ አሥተዳደር ሲደርሱ አቀባበል ተደርጓላቸዋል። የሰላም አማራጩን የተቀበሉት ታጣቂዎች በሕገ ወጥ ታጣቂዎች ውስጥ በመሪነት ሚና ሲሠሩ የነበሩ ናቸው።
ታጣቂዎቹ አንድ ብሬን ጨምሮ የተለያዩ ትጥቆች እና ተተኳሾችን ይዘው የሰላም አማራጩን እንደተቀበሉ የመካነ ኢየሱስ ከተማ አሥዳደር ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ ያሳያል።
መንግሥት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ የተቀበሉት ታጣቂዎቹ በቀጣይ ጫካ የሚገኙ ሌሎች ሕገ ወጥ ታጣቂዎች የሰላም አማራጩን እንዲቀበሉ በማድረግ የአካባቢው ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
