
የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ ማኅበራዊ ተቋማት እየተጎበኙ ይገኛሉ።
የሥራ ኀላፊዎቹ በከተማዋ የሚገኙትን ወንቃ መሠረታዊ ጤና ኬላ፣ የንጉሥ ተክለሃይማኖት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር እየተገነባ የሚገኘውን ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር የደብረ ማርቆስ መንገዶች ጥገና ዲስትሪክት የሕጻናት ማቆያ ማዕከል፣ ግሬስ የልጆች እና ቤተሰቦች ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች ተቋማትን ነው እየጎበኙ ያሉት።
የጉብኝቱ ዓላማ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት ጥንካሬዎችን እና ውስንነቶችን በመለየት ለሌሎች ተቋማት ተሞክሮዎችን ለማስተላለፍ እና ድጋፍና
ክትትል ለማድረግ እንደኾነ የተናገሩት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ናቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
