
የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) የክልሉን የመሠረተ ልማት ዘርፍ 1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም እና የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ውይይት አካሂደዋል።
ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) የመሠረተ ልማት ሥራዎች የሕዝብን ሕይወት በቀጥታ የሚደጉሙ ተግባራት የሚከወንበት መኾኑን ተናግረዋል። ዘርፉ የግንባታዎችን ደኅንነት የምንከታተልበት፣ የምንቆጣጠርበት፣ ሥራዎችን በፍጥነት እና በጥራት የምናሥፈጽምበት ተግባር ነው ብለዋል።
የመሠረተ ልማት ሥራ የአንድ ዘርፍ ሥራ ብቻ አይደለም ነው ያሉት። የክልሉ የኢኮኖሚ ለውጥ፣ የሕዝብ የኑሮ መሻሻል እና የመንግሥት የልማት ቃል ኪዳን በተግባር የሚረጋገጥበት እና ኀላፊነት ሚገለጽበት መኾኑንም ተናግረዋል።
የግምገማ አፈጻጸሙ ዓላማ የክልሉን የመሠረተ ልማት አቅጣጫ ለማረጋገጥ፣ የተገኙ ውጤቶችን ለማጠናከር፣ የታዩ ድክመቶችን ለመለየት፣ የአፈጻጸም እንቅፋቶችን ለመፍታት፣ ለቀጣዩ ሩብ ዓመት ግልጽ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እና ለመተግበር ያለመ ነው ብለዋል።
በፍጥነት በመሻገር ወደ ግንባታ መገባቱ፤ በመስኖ የጥናት እና ዲዛይን ሥራዎች መፋጠናቸው እና እንደ መገጭ ያሉ ፕሮጄክቶች ወደ መጠናቀቅ መቃረባቸው የታዩ ውጤቶች መኾናቸውንም አንስተዋል።
“ውጤቶች የሚታዩት ሥንሠራ ብቻ ነው” ብለዋል። የመሠረተ ልማት ሥራዎች የክልሉ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን የጀርባ አጥንት እና የልማት ሞተር መኾናቸውንም ገልጸዋል። ለመሠረተ ልማት ሥራዎች ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባም አሳስበዋል።
አንዳንድ ዞኖች እና ወረዳዎች ለመሠረተ ልማት በቂ ትኩረት አለመስጠታቸውን አንስተዋል። በቀጣይ መታረም እንዳለበትም አሳስበዋል።
ግፊት በማድረግ እየተፈጠሩ ያሉ የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ርብርብ ማድረግ ይጠበቃል ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
