የባሕር ዳር ከተማ የጽዳትና ውበት አብዮት – የ12ኛው የጣና ፎረም ዝግጅት!

10

 

ባሕር ዳር የጣና ዳርቻ ብቻ ሳትኾን፣ አሕጉር አቀፍ ሁነቶች የሚመከሩባት የትኩረት ማዕከልም ናት።

ከተማዋ ለ12ኛው የጣና ፎረም አምራ፣ ደምቃ እና ተሞሽራ ዝግጅቷን አጠናቅቃለች። በተከናወኑት የኮሪደር ልማት፣ የጽዳት እና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ድርብ ውበትን ተጎናጽፋለች።

የመንገዶቿ ዳርቻ አትክልት አብበዋል፤ ኮሪደሮቿም ድምቅ ብለው እንግዶቻቸውን ለመቀበል የደስታ ብርሃናቸውን እያበሩ ይገኛሉ። ተፈጥሮ እና የሰው ልጅ ጥበብ ተዋሕደውባት ባሕር ዳርን ከምንጊዜውም በላይ በውበት ላይ ውበት ደርበውባታል።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የአካባቢ፣ ጽዳት እና ውበት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጽጌረዳ አበበ ለ12ኛው የጣና ፎረም ከተማዋን ጽዱ፣ አረንጓዴ፣ ለእንግዶች ምቹ እና ለእይታ ማራኪ የማድረግ ሰፊ ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል። በከተማዋ ውበትን የሚያላብሱ አረንጓዴ አትክልቶችን እና ሳሮችን መሠረት በማድረግም የማስዋብ እና የአረንጓዴ ቦታዎችን የመንከባከብ ተግባራት በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ ነው ያሉት።

ይህንን ስኬታማ ለማድረግ በየዕለቱ ከ3 ሺህ 263 በላይ ሰዎች በመስክ በመሠማራት ለከተማዋ ውበት አበርክቶ እያደረጉ ነው።

ከተማዋ በምሽት በበቂ መብራት የተሸለመች እና ምንም ዓይነት የጨለማ ቦታ የሌለባት እንድትኾን ከአጋር ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሠራ እንደኾነም ነው የተናገሩት።

ይህም ወደ ባሕር ዳር የሚመጡ እንግዶች በከተማዋ ውበት ተስበው በቀጣይም ተመልሰው እንዲጎበኟት እና እንዲወዷት የሚያስችል መልካም ገጽታ እያፈራ ይገኛል ብለዋል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

ባሕር_ዳር_ጥቅምት_10_2019_ዓ_ም.

Previous articleለጤናው መስክ ‘የምሥራች’ የተባለው ቴክኖሎጂ ምን ይዞ መጣ?
Next articleየኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት – የሰላም እና የነፃነት ምልክት