በወገራ ወረዳ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ቡድኖች ወደ ሰላም ተመለሱ።

36
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ ገደብየ በተባለ አካባቢ በጫካ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የክልሉ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላም ተመልሰዋል።
ታጣቂዎቹን በሀገር መከላከያ ሠራዊት የ70ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሻለቃ እና የወረዳው መሪዎች ተቀብለዋቸዋል።
ወደ ሰላም የተመለሱት ታጣቂዎች በጫካ በቆዩበት ጊዜ ሕዝቡን ለእንግልት መዳረጋቸውን አምነዋል። ይባስ ብሎም በጫካ ያሉ ኀይሎች በቅርቡ ከክልሉ ሕዝብ ጠላቶች ጋር የመሰረቱት የጥፋት ጥምረት እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።
ከሕገ ወጡ ሕወሃት ጋር ትብብር በመፍጠር የአማራን ሕዝብ ጥቅም የሚጎዳ አካሄድ መከተላቸውን በመረዳታቸው ወደ ሰላማዊ መንገድ ለመመለስ መወሰናቸውንም ገልጸዋል።
በቀጣይም አባላቱ መንግሥት የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ተልዕኮ ለመቀበል፣ የበደሉትን ሕዝብ ለመካስ እና ለአካባቢው ሰላም ለመሥራት ዝግጁ መኾናቸውንም አረጋግጠዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“የኢትዮጵያ የደኅንነት ጋሻ”
Next articleኢትዮጵያ ከመጀመሪያው ጀምሮ የጣና ፎረምን ዋና ባለቤት ኾና እያስተናገደች ቀጥላለች።