“የጣና ፎረም እና ባሕር ዳር ለዓመታት የዘለቀ ትስስር አላቸው” አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር)

5
12ኛው የጣና ከፍተኛ የመሪዎች ፎረም ከጥቅምት 13/2019 ዓ.ም ጀምሮ በባሕር ዳር ይካሄዳል። መድረኩ በአፍሪካ የሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር እና ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎችን ለማምጣት መሠረት ያደረገ ነው።
በአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር) እንደተናገሩት ባሕር ዳር የጣና ፎረምን ለዓመታት በስኬት ስታስተናግድ ቆይታለች።
ጣና ፎረም እና ባሕር ዳር ለረጅም ዓመታት የዘለቀ ጠንካራ ትስስር አላቸውም ነው ያሉት። ከተማዋ የጣና ፎረምን በብቃት ስታስተናግድ ለጣና ፎረም ተሳታፊ መሪዎች፣ ምሁራን እና አጋር አካላት መገናኛ በመኾን እያገለገለች መኾኑንም አንስተዋል።
በዚህም በመላው አፍሪካ ሰላም እና መረጋጋት እንዲመጣ በውይይት እና በመተማመን ላይ የተመሠረተ መድረክ በማዘጋጀት ሚናን ለመወጣት ዕድል የሚፈጥር ስለመኾኑም አመላክተዋል።
የጣና ፎረምን ማስተናገድ ከተቋማዊ ኀላፊነት በላይ ትርጉም እንዳለውም ገልጸዋል። መድረኩ ዘላቂ ወዳጅነትን ለመገንባት እና ለአፍሪካ የወደፊት ጉዞ ጉልህ አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ታላቅ ዕድል ስለመኾኑም ጠቁመዋል።
✍️ ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበቴክኖሎጅ የዘመነ፣ ለሰንደቁ የታመነ!
Next article“እርስ በእርስ በመዋጋት የሚገነባ ሀገር የለም፤ አሁን ሰላምን መርጠናል” የሰላም አማራጭ የተቀበሉ ወጣቶች