
የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በወልድያ ከተማ ተካሂዷል።
የሰልፉ ተሳታፊዎች መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ሲል መስዋዕትነት እየከፈለ መቆየቱን ገልጸዋል።
ሰልፈኞቹ የወልድያ ከተማ ሕዝብ ከሠራዊቱ ጎን ኾኖ ደጀንነቱን በተግባር አረጋግጧል ነው ያሉት። ይህን ደጀንነት እና ድጋፍ እንደሚያጠናክሩም አረጋግጠዋል።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ታምራት ደምሴ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በደማቸው እና በአጥንታቸው ያጸኑትን ሰላም ለማስቀጠል ኅብረተሰቡ ድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
“ሀገራችን ኩሩ ኾና የቆመችው መከላከያ በከፈለው ደም እና መስዋዕትነት ነው” ብለዋል። የመከላያን መስዋዕትነት ዋጋ የምንከፍለው እንደ ሕዝብ ያስከበረልንን ሰላም በማጽናት እና በተቋማት የሥራ ድርሻችንን በአግባቡ በመወጣት የልማት አርበኞች ስንኾን ነው ያሉት ከንቲባው የከተማው ሕዝብ እና የመንግሥት ሠራተኞች የድርሻቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ወልድያ #ጥቅምት_07_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
