የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሕዝብ የቆመ የሀገር ኩራት ነው።

1

 

የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ደጀን ግርማው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የታሪካዊ ጠላቶቻችንን ዕኩይ ሴራ በማፍረስ ኢትዮጵያን ያጸና ነው ብለዋል።

የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጌትነት ጸጋዬ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ መስዋዕትነትን በመክፈል ሀገርን ያቆመ ጀግና ሠራዊት መኾኑን ተናግረዋል።

የደባርቅ ወረዳ አሥተዳዳሪ አበባው አዛናው በበኩላቸው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሕዝብ የሰጠውን አደራ በተግባር የሚፈጽም ድንቅ ሠራዊት ነው ብለዋል። የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት መደገፍ እንደሚገባም አንስተዋል።

የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎችም የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ኅብረ ብሔራዊነት የሚያሳይ፣ ከሕዝብ የወጣ እና ለሕዝብ የሚታገል የሀገር ኩራት እንደኾነ ገልጸዋል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ጎንደር #ጥቅምት_07_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ደረጀ ደርበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“መከላከያ ሠራዊታችን የሕዝብ ልጅ ነው”
Next articleሀገራችን ኩሩ ኾና የቆመችው በመከላከያ ሠራዊት ክንድ ነው።