“መከላከያ ሠራዊታችን የሕዝብ ልጅ ነው”

8

 

የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በደብረ ታቦር ከተማ ተካሂዷል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በሪሁን መንግሥቱ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ ሀገራት ሰላም የማስከበር ግዳጁን በኩራት የተወጣ ነው ብለዋል።

የሕዝብ ልጅ የኾነ እና ዛሬም እንደትናንቱ ለሀገሩ የቆመ ጀግና ሠራዊት እንደኾነ ነው የገለጹት።

ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ሕዝቡ ከሀገር መከላከያ ጎን በመሰለፍ ያሳየው ተነሳሽነት የሚደንቅ መኾኑንም ተናግረዋል። በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪን እንዲቀበሉም ጠይቀዋል።

​የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ ገብይ ኃይሌ (ዶ.ር) አብሮነትን እና አንድነትን አጠናክሮ ለማስቀጠል ለሰላም መረጋገጥ ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ ገልጸዋል። ሕዝቡ ለሀገር መከላከያ ደጀን በመኾን ያካሄደው የድጋፍ ሰልፍ የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ላሉ የሕዝብ ልጆች የሞራል ስንቅ መኾኑንም ተናግረዋል።

አሚኮ ያነጋገራቸው የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊ ወጣቶች ሰልፉ ሕዝቡ የሰላም ፍላጎቱን ያሳየበት እና ታጥቀው ጫካ ለሚንቀሳቀሱ አካላት የሰላም ጥሪ ያስተላለፈበት መኾኑን ተናግረዋል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ደብረ_ታቦር #ጥቅምት_07_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ተክለብርሃን ፈንታ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየታሪክ ባለቤቷ ጎንደር ለሀገር ጠባቂው መከላከያ ሠራዊት ያበሰረችው የድጋፍ ድምጽ
Next articleየኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሕዝብ የቆመ የሀገር ኩራት ነው።