
በሰሜን ወሎ ዞን በፍላቂት ገረገራ ከተማ አሥተዳደር እና በመቄት ወረዳ የሀገር መከለካያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በድጋፍ ሰልፉ:-
👉 የመከላከያ ሠራዊታችን የኅብረ ብሔራዊነታችን ማሳያ አርማችን ነው !!
👉 በማይነጥፈው የመከላከያ ሠራዊታችን የጀግንነት ተጋድሎ የሀገራችን ክብር ከፍ እናደርጋለን !!
👉 መከላከያ ሠራዊታችን፣ የፌደራል እና የክልል የጸጥታ ኃይሎች ለከፈሉት ዋጋ ክብር እንሰጣለን !!
👉 የኢትዮጵያ ጠላቶችን እየደመሰስን ሠንደቅ አላማችን ከፍ እናደርጋለን !!
👉 መንግሥት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች እንደግፋለን !!
👉 የሀገራችንን ሰላም ለማወክ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር የተሰለፉ ኀይሎችን በጽኑ እናወግዛለን !!
👉 የሀገራችን አንድነት በጸረ ሰላም ኀይሎች ሴራ አይደናቀፍም !!
👉 ሀገርን ለማጽናት እና ለማበልጽግ ከመንግሥት ጎን እንሰለፋለን !!
👉 ከግድቡ ወደ ወደቡ እንሸጋገራለን !!
👉 የባሕር በር ባለቤትነታችን በልጆቿ መስዋዕትነት እውን ይኾናል !!
👉 ለድል የተወለደው መከላከያ ሠራዊታችን አለኝታችን ነው !! የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።
