የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን ባሕር ዳር ገባ።

8

 

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን ባሕር ዳር ገብቷል። ከልዑካን ቡድኑ ጋር የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ (ዶ.ር) እና ሌሎችም የሚኒስቴሩ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ቡድኑ በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በክልሉ እና በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል።

ቡድኑ ወደ ባሕር ዳር የመጣው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄ ተከትሎ የባሕር ዳር ዓለም ዓቀፍ ስታዲዬምን ዝግጅት በተመለከተ ለመገምገም ነው።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_07_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበፍላቂት ገረገራ ከተማ አሥተዳደር እና በመቄት ወረዳ የሀገር መከለካያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
Next articleበገንዳ ውኃ ከተማ የሀገር መከለካያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።