ባሕር ዳር ለ12ኛው የጣና ፎረም ዝግጁ ናት።

2
የቱሪዝም ከተማዋ ውቢቱ ባሕር ዳር ከቀናት በኋላ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችን፣ አምባሳደሮችን እና ከፍተኛ ልዑካን ቡድኖችን ተቀብላ 12ኛውን የጣና ፎረም አህጉራዊ ጉባኤ ታስተናግዳለች። በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች እንግዶችን በላቀ ብቃት ለመቀበል ምን ሠሩ?
🏨 በባሕር ዳር የሚገኙ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ሥራ አሥኪያጆች እንደገለጹት እንግዶችን ለማስተናገድ ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል።
እንግዶችን ተቀብሎ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን መሥራታቸውን አንስተዋል።
አህጉራዊ ሥብሠባዎችን በጥሩ ሁኔታ ማስተናገድ የሆቴሎች ብቻ ሳይኾን የጠቅላላ ከተማዋ ጥረት ሊኾን ይገባል ነው ያሉት። በባሕርዳር ከተማ የሚገኙ ሁሉም የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት እና ነዋሪዎች እንደ ከተማ አምባሳደር ኾነው እንግዶችን ሊቀበሉ እንደሚገባ ተናግረዋል።
🚤 የሚሰጧቸው አገልግሎቶች ደረጃቸውን የጠበቁ መኾናቸውን ገልጸዋል። የጣና ፎረም እንግዶችን በጥሩ መስተንግዶ ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅቱን ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።
እንደ ጣና ፎረም ያሉ ትልልቅ ሁነቶች ከተማዋን፣ በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን እና ግለሰቦችን በልዩ ልዩ መንገድ ተጠቃሚ እንደሚያደርጉም ጠቅሰዋል።
🏛 የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ጋሻው እንዳለው ከአሚኮ ዲጅታል ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ባሕር ዳር ትልልቅ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶችን ማስተናገድ የሚችል ሁለንተናዊ አቅም ያላቸው ተቋማት ያሏት በመኾኗ ዝግጅቱ ሙሉ ነው ብለዋል።
እንዲህ ያሉ ትልልቅ ሁነቶች እና አህጉራዊ ፎረሞች በከተማዋ መካሄዳቸው ለከተማዋ የቱሪዝም እንቅስቃሴ መነቃቃት፣ ለንግድ ተቋማት ገቢ ማደግ እና ለኢንቨስትመንት መሳብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ነው ያሉት።
✍️ዘጋቢ፦ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየአማራ ክልል የኅብረተሰብ ተሳትፎ ማሥተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የአማካሪ ምክር ቤት አቋቋመ።
Next articleአትተንኩሷት፤ የተነኮሷት ሁሉ የሽንፈት ካባን ተላብሰው የሽንፈት ጽዋን ተጎንጭተዋልና።