የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ተሳትፎ ማሥተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የአማካሪ ምክር ቤት አቋቋመ።

1
የኅብረተሰብ ተሳትፎ አማካሪ ምክር ቤት ከክልል እስከ ወረዳ እንደሚቋቋም በተደነገገው መሠረት በክልል ደረጃ አማካሪ ምክር ቤቱ ተቋቁሞ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የአማካሪ ምክር ቤት አባል ቢሮ ኀላፊዎች የመጀመሪያውን ውይይት አካሂደዋል።
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኀላፊ አታላይ ጥላሁን አማካሪ ምክር ቤቱን ገንዘብ ቢሮ በበላይነት እንደሚመራው እና ተጠሪነቱም ለቢሮው መኾኑን ተናግረዋል። ይህም የሕዝብን ውሳኔ ሰጪነት፣ ልማት እና መልካም አሥተዳደርን በየደረጃው ለማረጋገጥ ወሳኝ እርምጃ መኾኑን ተናግረዋል።
አማካሪ ምክር ቤቱ በቀጣይ ጠንካራ እና የተደራጀ ሥራ ይጠበቅበታል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleለጡት ካንሰር በሽታ እንዳይጋለጡ ምን ያክል ክትትል ያደርጋሉ ? የጡት ካንሰር በዓለማችን በብዛት ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች ውስጥ ይመደባል።