
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል፡፡ በመደበኛ ስብሰባው አራት የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ነው የመከረው።
በተጨማሪም በሕገ- መንግሥቱ አንቀጽ 55/19 እና በምክር ቤቱ የአሠራር እና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 152 መሠረት የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ለመሰየም የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል።
የምክር ቤቱን ዋና እና ምክትል አፈ ጉባኤ፣ የመንግሥት ዋና እና ሁለት ረዳት ተጠሪዎች 13 አማካሪ ምክር ቤት አባላት ውሳኔ ቁጥር 2 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
በምክር ቤቱ የአሠራር እና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 4/1/(መ) እና አንቀጽ 5/4/(መ) መሠረት የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት፣ ተግባር እና ኀላፊነት ለመወሰን የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርጎ 13 ቋሚ ኮሚቴዎችን አጽድቋል።
እያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴ ዋና እና ምክትል ሠብሣቢ የሚኖሩት ሲኾን፤ ሠብሣቢዎቹ በአፈ ጉባኤው አቅራቢነት በምክር ቤቱ ተመርጠዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት ተግባር እና ኀላፊነት ለመወሰን የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ 03/2019 አድርጎ በሙሉ ድምጽም አጽድቋል፡፡
ዘጋቢ፦ ድልነሳ መንግሥቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
