የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ለ70 ማኅበራት የቤት መሥሪያ ቦታ አስረከበ።

11
የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ኅብረት ሥራ ማኅበራት ጽሕፈት ቤት የቤት መስሪያ ቦታ ተደራጅተው ለሚጠባበቁ ማኅበራት የዕጣ ማውጣት እና ርክክብ መርሐግብር አካሂዷል።
የቤት መስሪያ ቦታ የደረሳቸው የከሚሴ ከተማ ነዋሪዎች ተደራጅተው ከአስር ዓመት በላይ ሲጠባበቁ እንደነበር ገልጸዋል። አሁን ላይ የቤት መስሪያ ቦታ በማግኘታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።
በቤት ኪራይ ሲንገላቱ እንደነበር አንስተዋል። አሁን ላይ በተሰጣቸው ቦታ ደረጃውን የጠበቀ ቤት ገንብተው ለመግባት እንደሚሠሩ ገልጸዋል።
የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ኅብረት ሥራ ማኅበራት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኢብራሂም አብዱ ለዓመታት ተደራጅተው የቤት መሥሪያ ቦታ ሲጠባበቁ ለነበሩ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ቦታ ማስረከባቸውን ጠቅሰዋል።
በማኅበሩ የጸጥታ አካላት እና መምህራን ተጠቃሚ እንደኾኑም ገልጸዋል። የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሸሪፍ ቃሲም የቤት መሥሪያ ቦታ በከተማው የረጅም ጊዜ የመልካም አሥተዳደር ችግር እንደነበር ጠቅሰዋል። አሁን ላይ እልባት ማግኘቱን ተናግረዋል።
በቀጣይ የመሠረተ ልማት አውታሮችን በአጭር ጊዜ ለመገንባት ከተማ አሥተዳደሩ ይሠራል ብለዋል። የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ መንግሥት የዜጎችን የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ እየሠራ ነው ብለዋል።
ደረጃውን የጠበቀ ቤት መገንባት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ወታደራዊ ቁመናውን የሚያውቁት አይደፍሩትም፤ ይልቁንም ያከብሩታል”
Next articleየኮንፈረንስ ቱሪዝም በር ከፋች – ጣና ፎረም