
ባሕር ዳር: ጥቅምት 04/2019 ዓ.ም (አሚኮ) የጣና ፎረም በአፍሪካ የሰላም፣ የጸጥታ እና የደኅንነት ጉዳዮች ላይ በመወያየት አህጉራዊ መፍትሔዎችን ለመስጠት የተቋቋመ የምክክር መድረክ ነው።
መድረኩ አህጉራዊ ትስስርን ከመፍጠር ባሻገር የፖሊሲ አማራጮች የሚንሸራሸሩበት እና የዲፕሎማሲ እድሎች የሚሰፉበት ዓመታዊ ኹነት መኾኑን ጣና ፎረም ዶትኦርግ/tanafourm.org/ ላይ የተገኘ መረጃ ያሳያል።
ስለ ፎረሙ ምን እናውቃለን?
#የጣና ፎረም የመሪዎች ስብሰባ እ.አ.አ በ2009 የወጣውን የትሪፖሊ ሥምምነት ተከትሎ የተቋቋመ መድረክ ነው።
#የፎረሙ ዋና ዓላማ በአፍሪካ ላይ የሚስተዋሉ የጸጥታ፣ የሰላም እና የደኅንነት ኹኔታዎች ላይ በመወያየት አፍሪካዊ መፍትሔ ማፈላለግ ነው።
#መድረኩ እ.አ.አ ከ2011 ጀምሮ በባሕር ዳር ከተማ በየዓመቱ ይካሄዳል።
#እስካኹን ከተካሄዱት አስር ፎረሞች መካከል በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከተካሄደው የ9ኛው ፎረም በስተቀር ሁሉም በባሕር ዳር ከተማ የተካሄዱ ናቸው።
#12ኛው የጣና ፎረም በባሕር ዳር ከተማ ከጥቅምት 13 እስከ 15 ቀን 2019 ዓ.ም “በአፍሪካ የሰላም መንገዶች፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የጂኦ ፖለቲካ ለውጥ” በሚል መሪ ሐሳብ ይካሄዳል።
#ኢትዮጵያ ንቁ ተሳታፊ በመኾን ዲፕሎማሲዋን ታጠናክርበታለች ተብሎ ይጠበቃል።
#በዘንድሮው ፎረም የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ የተቋማት ኃላፊዎች፣ የቀድሞ መሪዎች እና በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኞች እንደሚገኙበት ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
