“የሳይበር ደኅንነት የሀገር ደኅንነት ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

3
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ “ንቁ ዜጋ፤ ደኅንነቱ ለተጠበቀ ሀገር!” በሚል መሪ መልዕክት የሚካሄደውን ሰባተኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደኅንነት ወር አስጀምረዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሳይበር ደኅንነት የሀገር ደኅንነት ነው ብለዋል።
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ያሳካናቸው የኢንተርኔት ተጠቃሚነት መስፋፋት፣ የቴሌኮም ዘርፉ ለውድድር መከፈት፣ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶች መስፋፋት እና የመንግሥት አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ የማቅረብ ርምጃዎች ለዲጂታል ሽግግር መሠረት መጣላቸውን ገልጸዋል።
ይህንን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ በማሸጋገር፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕያችንን እውን ለማድረግ እነ የቴክኖሎጂ ዕድገት የሀገራዊ ብልጽግናችን ወሳኝ ዐቅም እንዲኮን በሁሉም መስክ እየተሠራ ነው ብለዋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር የሀገራችንን የሳይበር ምኅዳር ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ በማድረግ፣ ለሀገራዊ ልማት፣ ለዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ስኬት እና ለላቀ ሀገራዊ ብልጽግና የሚያደርገውን የ24/7 ጥረት ዕውቅና መስጠት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የዲጂታል ምኅዳራችንን ከሳይበር ሥጋቶች መጠበቅ የሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነት፣ የዜጎችን ደኅንነትና የልማት ጉዟችንን የማስጠበቅ ጉዳይ ነው።
የዲጂታል ምኅዳራችንን የሚጠብቅ፣ የሀገራችንን ደኅንነት የሚያጠናክር እና የዲጂታል ወደፊት ጉዟችንን የሚያረጋግጥ ንቁ እና ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ መገንባት ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ጠላት ሰማይዋን ላይደፍረው፣ ምድሯንም ላይረግጠው የተዘጋጀ ጋሻ”
Next articleወርቅን ከስደት የመመለስ ጉዞ።