“ብሔራዊ አንድነት ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ መሠረት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

6

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሠንደቅ ዓላማ ቀንን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ‎“ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን”
‎
‎ብሔራዊ አንድነት ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ መሠረት ነው። ሠንደቅ ዓላማችንም የጋራ ታሪካችንን፣ ሉዓላዊነታችን እና በልዩነቶቻችን መካከል በጋራ የመቆም አቅማችንን የሚያስታውስ የብሔራዊ አንድነታችን ምልክት ነው ብለዋል።
‎
‎በዓድዋ የሀገሪቱ ሕዝቦች ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው በጋራ በመቆማቸው፣ በታላቅ ገድላቸው የዓለምን ትኩረት መሳብ ችለዋል። አባቶቻችን በፈተናዎች ከመከፋፈል ይልቅ አንድነታቸውን አሳይተዋል። ይህ በጋራ የመቆም ጥሪ መቼም ቢኾን ተቋርጦ አያውቅም፤ እያንዳንዱም ትውልድ ለዚህ ጥሪ እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል ነው ያሉት።
‎
‎መደመር ሁላችንንም አንድ ቀላል ጥያቄ ይጠይቀናል፤ እኛ የሀገራችንን እጣ ፈንታ ከዳር ቆመን የምንታዘብ ተመልካቾች ነን? ወይንስ “ይህች ሀገሬ ናት፤ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋም ያሳስበኛል” ማለት የምንችል ባለቤቶች?
‎
‎ቋንቋዎቻችን፣ ሃይማኖቶቻችን እና ማንነቶቻችን ለዘመናት በጋራ በምናልፍበት ታሪካዊ ጉዞ ውስጥ አብረው ተሰናስለው የተሸመኑ የአንድ ሸማ ክሮች ናቸው። ለሀገር መቆም ከትንንሽ የድፍረት እርምጃዎች ይጀምራል፤ ከራስ አልፎ ሰፊ ርዕይ ይዞ መሥራትንም ይጠይቃል። ያለፉት ትውልዶች ሀገሪቱን እንድንረከብ መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ ዛሬ በጋራ የምናጸናትን ሀገር ነው ለቀጣዩ ትውልድ የምናስተላልፈው።
‎
‎ስለኾነም ዛሬ ራስዎን ይጠይቁ፤ ለሀገርዎ አንድነት እና ብልጽግና ምን አበረክታለሁ? ብለዋል በመልዕክታቸው።

#የመደመር_መንግሥት

#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ፣ #ታላቅ_ርዕይ 🇪🇹🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_02_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleጠላትን በሩቅ የሚያሥፈራው የሠራዊቱ ዘመናዊ የድሮን አቅም።
Next articleከምድር ማሕጸን ወደ ሀገር ካዝና፤ የመንግሥት ስልታዊ አቅጣጫ!