
“ዓሳ አበላሻለሁ ዓባይ ዳር ነው ቤቴ” ተብሎ በሚዜምላት ውቧ ባሕር ዳር ከተማ የማለዳውን ፀሐይ ተከትለው በጣና ሐይቅ ዳር የሚሰማሩት ዓሳ አስጋሪዎች፣ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት እና ሳቢ የቱሪዝም መዳረሻዎች ናቸው።
ከማለዳዋ የፀሐይ ጮራ ጋር እኩል በጣና ሐይቅ ዳርቻ የሚገኙት ዓሳ አስጋሪዎች በሥራቸው ትጋት እና ብልሃት የበርካታ ሰዎችን ቀልብ በመሳብ ላይ ይገኛሉ።
አስጋሪዎቹ ሰፊውን መረባቸውን በብልሃት ወደ ሐይቁ እየወረወሩ ለሰዓታት በትዕግስት ሲቆሙ ይታያሉ።
አንዳንዴ መረባቸው በዓሳ ተሞልቶ ሲወጣ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ባዶ መረብን እየሳቡ በትዕግስታቸው እና በጽናታቸው ሥራቸውን ይቀጥላሉ።
ይህ በየማለዳው በጣና ዳርቻ የሚከናወነው ድንቅ የተፈጥሮ እና የሰው ልጅ ጥረት ውሕደት ባሕር ዳርን እና የጣና ሐይቅን ለመጎብኘት ከቅርብም ከሩቅም የሚመጡ ጎብኝዎችን ቀልብ የሚስብ እና የዐይን ማረፊያ ነው።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_30_2019_ዓ_ም
በያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
