የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናራንድራ ሞዲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።

7
የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናራንድራ ሞዲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናራንድራ ሞዲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በድጋሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ኾነው በመሾማቸው ነው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ያስተላለፉት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለሌላ የሥራ ዘመን ሥልጣን በመረከብዎ የተሰማኝን ደስታ እና መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ ብለዋል።
ባለፈው ወደ ኢትዮጵያ ያደረግሁትን ጉብኝት እና ያደረግነውን ሥብሠባ በደስታ አስታውሳለሁ ነው ያሉት። ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጠውም ገልጸዋል።
ትብብራችንን እና ወዳጅነታችንን የበለጠ ለማጎልበት ከእርስዎ ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ ነኝ ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የመደመር መንግሥት ካቢኔያቸውን በዛሬው ዕለት ለምክር ቤት ያቀርባሉ።
Next articleሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ሥብሠባውን እያካሄደ ነው።