የኢትዮጵያውያን የሥነ መንግሥት እሳቤ እስከምን ድረስ ነው?

4
ኢትዮጵያ ዓለም በጨለማ ውስጥ በነበረበት በዚያ ጊዜ የሥነ መንግሥት እሳቤ ያላቸው ሕዝቦች መኖሪያ ሀገር ናት።
ዓለም ገና ስለዴሞክራሲ እና የሰው ልጆች መብት ማውራት ሳይጀምር ኢትዮጵያውያን ግን በሀገር በቀል ጥንተ የሥነ መንግሥት ዕውቀቶች ሕዝብን ስታስማማ፤ ሀገረ መንግሥትም ስታጸና ኖራለች።
ዛሬም ሀገረ መንግሥት ለማጽናት ቀናኢ የኾነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈተናዎችን አልፎ እና ካርዱን ተጠቅሞ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመትከል ታትሯል። “አትመርጥም” ተብሎ ፈተና ቢገጥመውም “እምቢ መንግሥቴን የማጸናው በካርዴ ነው” በማለት ምርጫውን አካሄዷል።
ዛሬ መሥከረም 25/2019 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን ልዩ ቀን ናት። የከበዱ የሚመስሉ ፈተናዎች በሕዝብ እንደአለት የጠነከረ ብርቱ ፍላጎት ታልፈው የተመረጠ መንግሥት የሚቋቋምበት ቀን ነው።
በአሚናዳብ አራጋው
#ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!
#ባሕር_ዳር፡ መስከረም 25/2019 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleሴራ የማይጎትታት፤ የአፍሪካ ተምሳሌት
Next articleአካታች የፖለቲካ እና የትብብር ባሕል ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ