“የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ህያው ጋሻ”

6
እናት ሀገር ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ግርማዋ ብቻ ሳይኾን በልጆቿ ብረት በሚመስል ጽናት እና ወሰን በሌለው መስዋዕትነት የቆመች የጽናት ተራራ ናት።
ከሰማዩ ግርማ በታች በበረሃው አሸዋ እና በደጋው ቁር ውስጥ የሀገርን እና የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ሌሊቱን ሙሉ የሚተጉት የእነዚያ ጀግኖች ታሪክ ፤ የሰው ሕይወት፣ የእናት ፍቅር፣ የሀገር ፍቅር እና የመስዋዕትነት ህያው መከታ እንጂ።
ድንበር ተሻግሮ የዓለምን ሰላም ለማስከበር በተሄደበት እያንዳንዱ እርምጃ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ታሪክ ከሀገሪቱ ህልውና ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው።
ዛሬ ላይ ያ ታሪካዊ ጀግንነት በዘመናዊ ዕውቀት እና በቴክኖሎጂ ልህቀት ተጎናጽፏል፡
ሠራዊቱ የውጊያ ታክቲክን ከከፍተኛ ወታደራዊ አካዳሚዎች ዕውቀት ጋር በማቀናጀት የዘመኑን ሳይንስ የታጠቀ መኮንን እያፈራ ይገኛል።
ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን)፣ የራዳር ሥርዓቶች እና የሳይበር ደኅንነት መዋቅሮች የሀገሪቱን ሰማይ እና ድንበር አይደፈሬ አድርገውታል።
በሀገር ውስጥ የሚገኙ የመከላከያ ኢንዱስትሪዎች አነስተኛ እና መካከለኛ ጥይቶችን እንዲሁም የታጠቁ ተሽከርካሪዎችን በራስ አቅም በማምረት የሉዓላዊነታችንን መሠረት እያጠነከሩት ይገኛሉ።
የመሬት፣ የአየር እና የኮማንዶ ኀይሎች በቅንጅት ሲንቀሳቀሱ በማንኛውም መልከዓ-ምድር እና የአየር ሁኔታ ውስጥ የመብረቅ ያህል ፈጣን እና ወሳኝ ምላሽ የመስጠት የተቀናጀ አቅም ገንብተዋል።
የኢፌዴሪ የጦር ኀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንደገለጹት ዛሬ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በጽኑ መሠረት ላይ የሚያስጠብቅ ታላቅ ተቋም ገንብታለች።
በተለይም የአየር ወለድ እና ኮማንዶ ኀይል በአካል ብቃቱ፣ በጽናቱ እና በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቡ የውጊያን አቅጣጫ በቅጽበት የመቀየር አቅም ያለው የሀገር መከታ መኾኑን አብራርተዋል።
አስቸጋሪ እና ፈታኝ ሁኔታዎችን አልፎ ሀገራዊ አደራውን በብቃት የመወጣት አቅሙ ዛሬም ነገም ለሀገር ዋስትና መኾኑን አረጋግጠዋል።
ሀገር ማለት በድንበር ላይ የሚቆም ወታደር ብቻ ሳይኾን ያ ወታደር ደሙን እና አጥንቱን ሰጥቶ የሚጠብቃት የሁላችንም የጋራ ቤት ናት።
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleከቀጣናዊ ስጋቶች በላይ ከፍ ብሎ የተቀመጠው የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት!
Next articleየሻብያ ሴራ እና የኢትዮጵያ የማይናወጥ ጽናት