#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ ርዕይ!

4

 

የለማች እና ሰላሟ የተጠበቀ ሀገር መገንባት የሁሉም ኀላፊነት ነው።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከባለሃብቶች እና ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በወቅታዊ የሰላም እና የልማት ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ነው።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማዋ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ ብርሀን ንጉሤ የለማች እና ሰላሟ የተጠበቀ ሀገር መገንባት የሁሉም ኀላፊነት ነው ብለዋል።

መንግሥት የጀመረው የልማት እና የብልጽግና ጉዞ በአንድነት በመቆም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ተናግረዋል።

መንግሥት ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ከመገንባት ጎን ለጎን የሕዝብ ቁጥሩን እና በየጊዜው እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚ ሊሸከም የሚችል የባሕር በር እንዲኖር እየሠራ ይገኛልም ብለዋል። ሕዝቡ ሰላሙን ሊያውኩ የሚችሉ ጉዳዮችን በንቃት በመከታተል እና ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት በመሥራት የተለመደ ሀገር ወዳድነቱን መወጣት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

ዜጎች በችግር ውስጥ የሚኖሩበት ሁኔታ አብቅቶ ልጆች በነጻነት የሚጫወቱባት እና ወላጆች ያለስጋት የሚንቀሳቀሱባት ሰላማዊ ከተማን ለመፍጠር ሁሉም በጋራ መትጋት አለበት ብለዋል።

#አሚኮ #የሀገር_ሉዓላዊነት_ሰላም #ኢትዮጵያ🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_22_2019_ዓ_ም

‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article‎ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ 🇪🇹
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።