
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብታዊ፤ ልማታዊ ዕድገት እና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ቀጣይነት ባለው መንገድ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር በላቸው ፀሐይ በአንድ ወቅት ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ሀገሪቱ ወደ ዲጂታላይዜሽን እና ወደ ስማርት ሲቲነት ለመቀየር በከፍተኛ ግስጋሴ ላይ እንደምትገኝ መግለጻቸው ይታወሳል።
መንግሥት ለዲጂታላይዜሽን ጉዞ መሠረት የኾኑ ዘርፈ ብዙ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ሥራዎችን ያከናወነ ሲኾን ዜጎች ከቴክኖሎጂው ጋር አብረው መራመድ የሚችሉበትን ዕውቀት እና ክህሎት እንዲያገኙ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡
ለአብነትም የኢትዮ-ኮደርስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ሥልጠናን አንስተዋል። የተለያዩ ተቋማት የቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸውን በማስፋት የመንግሥት አገልግሎቶችን፤ የንግድ ሥርዓቶችን እና የዜጎችን የዕለት ከዕለት ኑሮ እንዲያዘምኑ መንገድ መክፈቱንም ተናግረዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ይፋ መደረጉ ለዚህ ለውጥ ትልቅ አጋዥ እንደኾነ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ከለውጦች መካከል
የኢትዮቴሌኮም ዘርፍ አንዱ ነው። የ4G እና 5G ኔቶርኮች መስፋፋትም የዚሁ ውጤቶች ናቸው። የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትም ሌላው ለውጥ እንደኾነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መረጃ ያስረዳል።
ይህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ወደ መደበኛው የፋይናንስ ሥርዓት አስገብቷል። የብዙዎችን እንግልትም ቀንሷል፤ ቀልጣፋ የገንዘብ ልውውጥ እንዲኖርም አድርጓል።
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ!
