
በጀናሞራ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።
በሰሜን ጎንደር ዞን ጃናሞራ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉት ታጣቂዎች ከ130 በላይ ናቸው። የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች መንግሥት ለፈጸምነው ስህተት ይቅርታ በማድረጉ እና በድጋሜ እድል ስለሰጠን እናመሰግናለን ብለዋል።
የሀገር ሽማግሌዎችን ፍርድ ለማክበር እና የበደልነውን ሕዝብ ይቅርታ አድርግልን ለማለት ዝግጁ ነን ነው ያሉት።
የጃናሞራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት
የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ራድያ ነሲቡ መንግሥት የበደላችሁትን ጥፋት እንድትማሩበት ምኅረት አድርጓል ብለዋል። በማወቅም ኾነ ባለማዎቅ በሕዝባቹሁ ላይ ላደረሳቹሁት ጥፋት ዝቅ ብላቹሁ ይቅርታ መጠየቅ ፣ እርቅ በመፈጸም እና ወደ ቀድሞ ሰላማዊ ሕይወታችሁ ልትመለሱ ይገባል ነው ያሉት።
ከጃናሞራ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው እናንተ ወልዶ ላሳደጋቹሁ ሕዝብ ስጋት ከመኾን ይልቅ ትልቅ አቅም እና ደጀን መኾን አለባችሁ ብለዋል። እንደ አባቶቻቸው ለሀገር ዋልታ መኾን እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
#ታላቅ_ሀገር #ታላቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
#ባሕር_ዳር #መስከረም_19_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
