የሀገር ባለውለታዎችን ማክበር እና ዘላቂ ደኅንነታቸውን ማረጋገጥ ይገባል።

12

 

በደብረ ታቦር ከተማ “እንክብካቤ እና ዘላቂ ደኅንነት ለአረጋውያን መልካም ሕይወት” በሚል መሪ መልዕክት 35ኛው ዓለም አቀፍ የአረጋውያን ቀን በፓናል ውይይት ተከብሯል።

በከተማዋ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ በተዘጋጀው በዚህ መርሐ ግብር የሥራ ኀላፊዎች፣ የአረጋውያን ማኅበር ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ደበበ አክሎግ እና የደብረታቦር ከተማ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ያየሽ ደረስ አረጋውያን የኅብረተሰቡ እሴቶች ማኅደር እና ሀገር የገነቡ ታላቅ ባለውለታዎች መኾናቸውን ገልጸዋል።

መንግሥት እና አጋር አካላት ለአረጋውያን ተገቢውን እንክብካቤ፣ የደኅንነት ከለላ እና ማኅበራዊ ዋስትና ለማረጋገጥ በቅንጅት እየሠሩ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር አረጋውያን ማኅበር ሠብሣቢ መንግሥቱ አይቸው ቀኑን ከማክበር ባለፈ ለአረጋውያን የጤና፣ የማኅበራዊ እንክብካቤ እና የሰብአዊ መብት ከለላ ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ማኅበሩ በአሁኑ ወቅት በደን ልማት እና በግብርና ሥራዎች እየተሳተፈ መኾኑን ገልጸዋል። ወጣቱ ትውልድ የሀገርን አንድነት እና ዳር ድንበር የመጠበቅ ኀላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

#አሚኮ #የአረጋውያን_ድጋፍ #አማራክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

#ደብረታቦር #መስከረም_19_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ:- ተክለብርሃን ፈንታ
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleከተሳሳተ መረጃ መራቅ እና እውነትን መከተል ይገባል።
Next articleየአማራ ክልል ፍርድ ቤት የዳኞች ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል።