ከተሳሳተ መረጃ መራቅ እና እውነትን መከተል ይገባል።

9

 

የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በልማት፣ በሰላም እና በጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መክሯል።

በምክክሩ የተሳተፉ የከተማዋ ነዋሪዎች የወልድያ ከተማን ሰላም ለመጠበቅ ኀላፊነታቸውን እየተወጡ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ይህንን ተግባር እንደሚያስቀጥሉም አረጋግጠዋል።

የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ መንግሥት ከተማዋን የማዘመን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። ልማት ሰላምን ይሻል ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ኅብረተሰቡ የከተማዋን ሰላም በብሎክ አደረጃጀት እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀብታሙ ሞገስ ማኅበረሰቡ ከተሳሳተ መረጃ ራሱን መጠበቅ እንዳለበት ገልጸዋል። ትክክለኛ የመረጃ ምንጭን በመከተል የአካባቢውን ሁለንተናዊ ልማት እና ሰላም እንዲያስቀጥልም ጠይቀዋል።

የአማራ ክልል ኘላን ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ምትኩ ዓለማየሁ (ዶ.ር) ኅብረተሰቡ ከጸጥታ መዋቅሩ ጎን በመቆም አብሮነቱን እንዲያጸና ጠይቀዋል።

በተሳሳተ መንገድ ወደ ጥፋት የገቡ ልጆቹን መክሮ እንዲመልስም አስገንዝበዋል።

#ወልድያ #መስከረም-19_2019 ዓ.ም

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleወጣቶች ሰላምን ለማረጋገጥ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ተቀናጅተው ሊሠሩ ይገባል።
Next articleየሀገር ባለውለታዎችን ማክበር እና ዘላቂ ደኅንነታቸውን ማረጋገጥ ይገባል።