
በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከሚሴ ከተማ በወቅታዊ የሰላም እና የመልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ የሰላም መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የተሳተፉ የከሚሴ ከተማ ወጣቶች ሰላምን ለማስፈን በመደራጀት እና የአካባቢያቸውን ሰላም ለማረጋገጥ ከመንግሥት ጋር በቅንጅት እየሠሩ መኾናቸውን ጠቅሰዋል።
ወጣቶቹ በአካባቢያቸው ሰላም እና የልማት ሥራዎች የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።
የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ አሊ ሰይድ የከተማዋን ሰላም እና ልማት ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መኾኑንም ገልጸዋል።
የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሸሪፍ ቃሲም ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላም ለማረጋገጥ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ተቀናጅተው ሊሠሩ ይገባልም ብለዋል።
በቀጣይ በሚሠሩ የሰላም እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ወጣቶችን ለማሳተፍ ጥረት እንደሚደረግ አብራርተዋል።
#አሚኮ #ሰላም #አማራክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ከሚሴ #መስከረም_19_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
