ባሕር ዳር በዋልያዎቹ ደጋፊዎች ደምቃለች።

7

 

ሰዓታት በቀሩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) እና የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ለመታደም የዋልያዎቹ ደጋፊዎች በጉጉት እየተጠባበቁ ነው።

ዋሊያዎቹ ከጠንካራው የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያደርጉት ይህ ጨዋታ በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቅ ነው።

ከተማዋ በሁሉም አቅጣጫ በሀገር ፍቅር ስሜት በተሞሉ፣ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ባነገቡ እና የብሔራዊ ቡድኑን ማሊያ በለበሱ ደጋፊዎች ተሞሽራለች።

ደጋፊዎቹ በከፍተኛ ሞራል ስፖርታዊ ዘፈኖችን እያቀነቀኑ የተለያዩ የድጋፍ ድምጾችን እያሰሙ እና በጋራ ኾነው እያዜሙ ይገኛሉ።

የደጋፊዎች ከፍተኛ የጉጉት ስሜት የጨዋታውን ግለት ከወዲሁ ጨምሮታል። የባሕር ዳር ከተማ አጠቃላይ እንቅስቃሴም ወደዚሁ ታላቅ ስፖርታዊ ክንውን አቅጣጫ ዙሯል።

በስታዲየሙ ዙሪያ ያለው ደማቅ ድባብ የኢትዮጵያውያንን ጥልቅ የእግር ኳስ ፍቅር እና ሀገራዊ ስሜት በጉልህ የሚያሳይ ነው።

በአሁኑ ሰዓትም ደጋፊዎች ቦታቸውን ለመያዝ ወደ ስታዲየሙ መግባት ጀምረዋል።

#AMECO #FootBall #Bahirdarint’Stadium #ኢትዮጵያ🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_19_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ:- ስማቸው አጥናፍ
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየጤና ተቋማትን አቅም በማሳደግ የመድኃኒት አቅርቦት ችግርን መፍታት ይገባል።
Next articleትብብር እና አንድነትን ማጠናከር ይገባል።