“ትግሉ ዓላማ የሌለው መኾኑን ተረድተናል” የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች

12
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች ትግሉ ዓላማ የሌለው እና ለሕዝብ የማይጠቅም መኾኑን ተረድተናል ብለዋል። አሁን ያለው የትጥቅ እንቅስቃሴ አዋጭ አለመኾኑን መገንዘባቸውንም ገልጸዋል።
አሁንም በጫካ የሚገኙ ሌሎች ታጣቂዎች ትግሉ ፋይዳ የሌለው መኾኑን ተረድተው የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ከታች አርማጭሆ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎችን በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የወረዳ እና የዞን የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“በጠንካራ ተቋማት ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ያላት ኢትዮጵያን እየገነባን እንቀጥላለን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleየጤና ተቋማትን አቅም በማሳደግ የመድኃኒት አቅርቦት ችግርን መፍታት ይገባል።