
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ ወረዳ ሮቢት ቀጣና በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
የሰላም አማራጭ የተቀበሉትን ታጣቂዎች የላይ አርማጭሆ ወረዳ የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሰላም አማራጭን መቀበል ለግለሰቦችም ኾነ ለማኅበረሰቡ የሚጠቅም አማራጭ መኾኑ ተገልጿል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉት ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ኑሮ እንዲቀላቀሉ የሚያግዙ ሥራዎች እንደሚከናወኑ የወረዳው የሥራ ኀላፊዎች ተናግረዋል።
ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የሰላም አማራጭን የተቀበሉት ታጣቂዎችም የሰላም አማራጭን መቀበላቸው ለቀጣይ ሕይወታቸው አዲስ አቅጣጫ እንደሚፈጥርላቸው ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ!
