
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባሕል እና በሃይማኖታዊ እሴቶች የበለጸጉ በርካታ የቱሪዝም ሀብቶች ያሏት ሀገር ናት።
የኢትዮጵያ የቱሪዝም ሀብት ሰፊ አማራጮችን እና ጸጋዎችን ያካተተ ነው።
ከደጋ እስከ ቆላ የሚያካልል ሥነ ምኅዳር፣ ከከፍተኛ ሙቀት እስከ ቅዝቃዜ የሚደርስ የአየር ንብረት እና ከራስ ደጀን እስከ ዳሎል የሚዘልቅ ውብ መልከዓምድር የሀገሪቱን የብዝኀ ቱሪዝም ጸጋን በግልጽ ያሳያል።
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የሐረር ጀጎል ግንብ፣ የጎንደር አብያተ መንግሥታት፣ የአክሱም ሐውልት፣ የሶፍ ዑመር ዋሻዎች እና ሌሎች በርካታ አስደናቂ የባሕል እና የታሪክ ሀብቶችም ለኢትዮጵያ ቱሪዝም መሠረት ናቸው።🏰
በተጨማሪም ከ6ሺህ በላይ ለሚኾኑ የዕፅዋት ዝርያዎች፣ እንደ ዋሊያ አይቤክስ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ እና ቀይ ቀበሮ ያሉ ብርቅየ እንስሳትም ባለቤት ናት።🌿
እነዚህ ተፈጥሯዊ እና ባሕላዊ ጸጋዎች ተደምረው ኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ የቱሪስት መዳረሻ እና በቱሪዝም ዘርፍ ሀብታም እንድትኾን አስችሏታል።🌳🦅
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ትኩረት ሰጥታ በመሥራቷ ተጨባጭ ለውጦችን አስመዝግባለች።
🎯 ሀገሪቱን ተወዳዳሪ እና አስተማማኝ የቱሪስት መዳረሻ የማድረግ ራዕይም ተሰንቋል። በዚህም መንግሥት ጸጋዎቿን ወደ ኢኮኖሚ ለመቀየር የሚያስችሉ የፖሊሲ ለውጥ አድርጓል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ ሰባት አዳዲስ የአውሮፕላን ማረፊያዎች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል።✈️
በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ እና በመሰል መርሐ ግብሮች አማካኝነት በሀገር አቀፍ ደረጃ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች ተገንብተዋል። ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የሥብሠባ ማዕከላት፣ መንገዶች እና የዲጂታል መሠረተ ልማት ሥርዓቶች ተዘርግተዋል።🌐🛣️
ለቱሪዝም መሠረት የኾኑ እና ተጎድተው የነበሩ በርካታ ታሪካዊ ቅርሶች ተጠግነው ለጉብኝት ክፍት ኾነዋል። ወደ ውጭ ሀገር ሸሽተው የነበሩ በርካታ ቅርሶችም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተደርጓል።
📌በ2018 በጀት ዓመት ብቻ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ የዓለም አቀፍ ጎብኝዎች ሀገሪቱን ጎብኝተዋታል። ከዚህም 5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።
📌በተመሳሳይ ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥ ያሉ ቦታዎችን ጎብኝተዋል። ይህም ካለፈው ዓመት በ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ጭማሪ ያሳየ ነው። ከ79 ቢሊዮን ብር በላይም ገቢም አስገኝቷል።
📌በኮንፈረንስ ቱሪዝምም አዲስ ስኬቶችን እያስመዘገበች ትገኛለች። በበጀት ዓመቱ ኢትዮጵያ 204 የዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በስኬት ማስተናገድ ችላለች። ይህም ካለፉት ሁለት ዓመታት በ166 ብልጫ አሳይቷል።
#አሚኮ #Tourism #Ethiopia🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_12_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
