
በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ ማርብል እና ግራናይት የሚያመርተውን የወረታ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ፣ አማጋ ጨርቃጨርቅ ማምረቻ ፋብሪካ፣ ገደፋው ይስማው አውቶሞቲቭ እና ትሬለር ማኑፋክቸሪንግ፣ በአማራ ማሽነሪ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የባሕርዳር ጄኔራል ፍሌክሴብል እና ፋውንደሪ ፋብሪካ፣ ቋሪት አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር እና አሜን የምግብ ዘይት ፋብሪካን ነው የጎበኙት።
ባሕር ዳር ከተማ በርካታ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙባት ለኢንቨስትመንት የተመቸች ከተማ ናት። በከተማዋ ለኢንቨስትመንት ዘርፉ በተሰጠው ትኩረት በርካታ ኢንዱስትሪዎች በምርት ላይ ናቸው።
መንግሥት ባለፉት ዓመታት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ለውጥ እየተመዘገበ ነው። በአማራ ክልል የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች የክልሉን እና የሀገሩቱን የኢኮኖሚ አቅም ከፍ የሚያደርጉ ናቸው። ለበርካታ ወገኖችም የሥራ እድል ፈጥረዋል።
#አሚኮ #ባሕርዳር #አማራክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_09_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
