
የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በክልሉ በክረምት በጎ ፈቃድ አማካኝነት የተከናወኑ ተግባራትን ገምግሟል።
የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጌቱ ወዬሳ በክልሉ በክረምት በጎ ፈቃድ 209 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የዜጎችን ችግር ያቃለሉ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።
ሀገር የሚገነባው እያንዳንዱ ዜጋ የራሱን ድርሻ ሲወጣ እንደኾነም ገልጸዋል።
አንድ ወጣት ጊዜውን ሲሰጥ፤ አንድ ባለሙያ ዕውቀቱን ሲያካፍል፤ አንድ ዜጋ የተቸገረን ወገን ሲደግፍ፤ አንድ ሰው አካባቢውን ሲያጸዳ ወይም ችግኝ ሲተክል እነዚህ በተናጠል ትንሽ የሚመስሉ ተግባራት በሚሊዮኖች እጅ ሲደረጉ የሀገር ግንባታ ይኾናሉ ነው ያሉት።
በዚህ መርህ የምንከውነው የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባር የአንድ ወቅት ዘመቻ ብቻ ሳይኾን በመረዳዳት እና በመተባበር የሀገር ፍቅርን በተግባር የምናሳይበት መድረክ ነው ብለዋል።
ወጣቶች፣ ባለሙያዎች፣ ተማሪዎች፣ የሀገር አገልጋዮች እና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን እና ዕውቀታቸውን ለማኅበረሰብ እያበረከቱ እንደኾነ አንስተዋል።
የምንሠራው በጎ ተግባር ዛሬ ላይ የዜጎችን ችግር ከመፍታት ባሻገር ለነገ ትውልድ የመተባበር እና የመረዳዳት ባሕልን የሚተክል በመኾኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በአንድነት የጀመርነውን የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባር በክረምት ሳንገድበው በየቀኑ እና በየቦታው የምንኖረውን የመረዳዳት ባሕል እንገንባ ነው ያሉት።
#ባሕር_ዳር #መስከረም_08_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
