በጃናሞራ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።

10

 

በሰሜን ጎንደር ዞን ጃናሞራ ወረዳ ባርና እና ማሬ ወንዝ ቀበሌዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 56 ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።

የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎችን የደባርቅ፣ የጃናሞራ ወረዳ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና እና በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እዝ መሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እዝ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ዳምጠዉ ዘነበ ሰላምን መርጣችሁ ወደ ሕዝብ በመቀላቀላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። ሌሎች ታጣቂዎችም የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል።

የጃናሞራ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ሸጋው ተሰማ መንግሥት በሆደ ሰፊነት ላጠፉት ጥፋት ይቅር ማለቱን ገልጸዋል። የተገኘውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሰላማዊ ኑሯቸውን ሊመሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። እርስ በርስ መገዳደል የሚያስከትለዉ መዘዝ ከባድ መኾኑን ገልጸዋል።

ከሰሜን ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎችም ጦርነትን በመጥላት ሰላምን መምረጣታቸውን ገልጸዋል። ሰላምን በመስበክ ወደ ቀያቸዉ እንዲመለሱ ያደረጓቸውን የአካባቢው መሪዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና የመከላከያ መኮንኖች አመስግነዋል።

Previous article“ምክር ቤቶች የጠንካራ ሀገር መሠረቶች ናቸው” ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
Next articleሀገር የሚገነባው እያንዳንዱ ዜጋ የራሱን ድርሻ ሲወጣ ነው።