ከግብርና ማዘመን እስከ ዘላቂ ሰላም

3

 

የምሥራቅ ጎጃም ዞን የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸምን በመገምገም፣ በ2019 በጀት ዓመት በግብርና ምርታማነት፣ በመልካም አሥተዳደር እና በሰላም ግንባታ ላይ ያተኮሩ ሰፋፊ ዕቅዶችን ማቀዱን አስታውቋል።

የምሥራቅ ጎጃም ዞን አሥተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑ በመድረኩ እንደገለጹት በተያዘው በጀት ዓመት የቡና፣ የአቮካዶ፣ የማንጎ፣ የደጋ እና ቆላ ፍራፍሬዎችን አቅም በስፋት በመጠቀም የግብርና ምርታማነትን እና አሠራርን ለማዘመን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራል ብለዋል።

በ2018 በጀት ዓመት ሰላም ከማስከበር በተጓዳኝ በግብርና ልማት እና ኢንቨስትመንትን በማነቃቃት አበረታች ተግባራት መከናዎናቸው ተገልጿል።
በ2019 በጀት ዓመት ደግሞ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ እና የዞኑን ሕዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ኾኖ ተቀምጧል።

አሚኮ ያነጋገራቸው የመድረኩ ተሳታፊዎች ኅብረተሰቡ በገንዘብ እና በጉልበት የሚያደርገውን ድጋፍ በማቀናጀት በልማት እና በመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ካለፈው ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል።

በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች ዕውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

#አሚኮ #ምሥራቅጎጃም #ልማት #ሰላም #ኢትዮጵያ 🇪🇹

#ደብረ_ማርቆስ #መስከረም_08_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ዘላለም አስፋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleፈተናዎች ያበረቷት ተማሪ ሶሊያና ማሩ
Next article“ምክር ቤቶች የጠንካራ ሀገር መሠረቶች ናቸው” ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ